በውጭ ሀገር የተወለዱ ልጆች ወላጅ እንደመሆናቸው መጠን ልጆቻችንን አማርኛ በማስተማር ባህላቸውንና ማንነታቸውን በጥልቀት እንዲያውቁ እንጥራለን::
ከዚያም በተጨማሪ ልጆቻችን ከአያቶቻቸዉ እንዲሁም ኢትዮጵያ ከሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር በቀላሉ መግባባት እንዲችሉ እና ማንነታቸውን አውቀው በራስ መተማመንን እንዲያጐለብቱ ከልብ የመነጨ ፍላጐት አለን!!
ሆኖም ግን በተለይ በውጭ ሀገር የሚገኙ ልጆችን አማርኛ ለማስተማሪያ የሚሆኑ መፅሀፎች ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኖ አግኝተነዋል ስለዚህም ታዳጊዎችን  በቀላሉ በሚስብ እና በጨዋታ መልኩ የተዘጋጀ መፅሐፍ ይዘንልዎት ቀርበናል::
በተለየ መልኩ የተዘጋጀው መፅሀፋችን ልጆች እየተዝናኑ እንጂ ቃላትን እየተማሩ ሳይመስላቸው ብዙ ቃላትን በአጭር ጊዜያት ውስጥ እንዲማሩ ያግዛቸዋል::

የራሳችን ልጆች መጽሀፉን ሲጠቀሙ የነበራቸው ደስታ እና በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ያሳዩት ለውጥ ለእናንተም ልጆች እንዲሆን ብለን ይህንን መፅሀፍ በታላቅ ደስታ አቅርበንልዎታል::